EthiopianTender.com owned by Beri General Trading PLC
Home About Us FAQ Sample Tender Post Bid/Tender Register Login Telegram Call Us

Tender Details

Source: አዲስ ዘመን ህዳር 1,2019 የተለጠፈበት ቀን: November 11, 2026 የሚዘጋበት ቀን: November 16, 2026

Source: አዲስ ዘመን ህዳር 1,2019

Posted Date: November 11, 2026

Tender Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኮምቦቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የ2019 በጀት አመት የሚያስፈጉ

* ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ /የቢሮ አላቂ ዕቃዎች

* ሎት 2 የተለያዩ ህትመቶች

* ሎት 3 የጽዳት እቃዎች

*ሎት 4 የደንብ ልብሶች

*ሎት 5 የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች

* ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸርና ሌሎች /

*ሎት 7 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን/ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን / በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TN Number/ ያላቸው

3. የአገልግሎት መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 13 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር መወዳደር ለሚፈልጉት እያንዳንዱ ሎት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ/ ብር በመከፈል ከግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ከፍል ቢሮ ቁጥር 22 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው

8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት እሰከ 6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ ነገር ግን 6ኛው ቀን የስራ ቀን ካለሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 4፡00 የጨረታ ሰነድዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. ጨረታውን የምናወዳድረው የጽህፈት መሳሪያን፤ህትመትን የጽዳት እቃዎችን እና የደንብ ልብሶችን በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ሲሆን ኤሌክትሮኒከስና ቋሚ እቃዎችን በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡

10. የዕቃውን ማንኛውንም ማጓጓዣ ወጪ ችሎ ኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፣

1. የደንብ ልብስ አሸናፊው የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡

12, የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

13.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

14.በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 28 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0335547 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት