Source: አዲስ ዘመን (NOV 12, 2026)
Posted Date: November 12, 2026
የአሸዋ አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ ፕሮጀከቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ጥራቱን የጠበቀ አሸዋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ጥራቱን የጠበቀ አሸዋ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1.ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
3. ጥራት ያለው አሸዋ በበቂ ሁኔታ ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት በዋናው መ/ቤት በሚገኘው ግዥ መምሪያ ብር 230.00 /ሁለት መቶ ሰላሣ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ እና የፋይናንሻል ኘሮፖዛላቸው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6. ጨረታው ህዳር 10/2019 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ቀን 9፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
7. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:-
ፍላጎት ያላችሁ አመልካቶች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኢምፔሪያል አደባባይ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ዲ ኤች ገዳ ቀለም ፋብረካ ጀርባ ባለው ዋናው መ/ቤት ግዥ መምሪያ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛትም ሆነ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ስልክ ቁጥር :-0116-62-03-57 ወይም 0116-18-94-85
ሞባይል 0912-100824
አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል
This is a sample tender. To access all active tenders and full details:
Subscribe Now