Source: አዲስ ዘመን (November,13,2026)
Posted Date: November 13, 2026
የኢትዮጵያ ባዮሜትሪከስ ማኅበር (Ethiopian Biometric Society) በ1993 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ማኅበር ነው። ማኅበሩ ለሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) አገልግሎት ብቁ የሆኑ የኦዲት ድርጅቶችን ለመጋበዝ ይህን ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡።
1. የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
2. በሙያ ብቃትና ሕጋዊነት ታውቀው በመንግሥት የተመዘገቡ፤
3. የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
4. በኦዲቲንግ ሥራ ልምድ ያላቸው፤
5. የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ሰርተፊኬት ያላቸው፤
6. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን አለበት፡፡
ተወዳዳሪዎች ለኦዲት አገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋና ሥራውን ሠርታችሁ የምታስረከቡበትን ቀን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሙያ ደረጃችሁንና ሕጋዊነታችሁን የሚገልጹ ማስረጃዎች _ በማያያዝ ከታች በተጠቀሰው የማኅበሩ አድራሻ እንድታመለክቱ እናስታውቃለን፡፡
አድራሻ፦ አዲስ አራት ኪሎ ንግድ ማዕከል፣
4ኛ ፎቅ፣
ቢሮ ቁጥር G-04-1
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር፦ 0993916717/0911418062
This is a sample tender. To access all active tenders and full details:
Subscribe Now